ምስጋና ምስጋና ይለኛል ዘምር ዘምር ይለኛል አምልክ አምልክ ይለኛል ጌታዬ ይገባዋል እጅግ የበዛውን የእርሱን ምህረት ማለዳ ማለዳ መቀበል ከእርሱ ፊት ምስጋናን መጨመር እለት እለት አስለምዶኛል ለክብሩ መቀኘት ምስጋና መልካም 3X አምልኮ መልካም 3X ዝማሬ መልካም 3X ድል ማድረጊያ ጎዳና አሃሃ 1 ከማመስገን ጋር በፀሎት ለሚቆየው በአንተ ፊት በችግር ውስጥም ላመሰገነህ አብልጠህ መልካም ታደርጋለህ ስለ ምህረትህ ስለጥበቃህ ስለውለታህ ምስጋና መልካም 3X... በችግር በደስታ በመከራ ምስጋና መልካም 3X... 2 ወደጉድጓድ ቢጣልም ምስጋና አለ ተላልፎ ተሽጦም ምስጋና አለ ፀሎትም ቢዘገይ ምስጋና አለ ከሚያመሰግን ጋር ኢየሱስ አለ ምስጋና መልካም.... 3 ስለሆነው ብቻ አይደለም ስለተደረገው በሁሉ ጌታን ማመስገን መልካም ነው የድልም ሁሉ ሚስጥር ማሸነፊያው ምስጋና ነው የተዘጋውን ማስከፈቻው ድል ማድረጊያው ይብዛ ይብዛ ምስጋናው ይጨመርለት እልልታው ቤቱን ይሙላው ደመናው እየበዛ ክብር ሙገሳው